This course is Under Construction : Come Back Later
ኮረናን ተከትሎ በነበረው ጊዜ የኢትዮጵያ ስራ ያለማግኘት ደረጃ (unemployment rate) ከ3.2 ፐርሰንት በላይ ደርሶ ነበር። አሁን የተወሰነ መሻሻል ቢታይበትም ሃገራችን ውስጥ በተከሰቱ ሁኔታዎች ቁጥሩ አሁንም ከ2.5 ፐርሰንት በላይ እንደሆነ ይገመታል።
ይህ ቁጥር በአሃዝ ሲሰላ አስደንጋጭ ነው።
በዚህም ምክንያት ስራ ፍለጋ የዘመኑ ወጣቶች ፈተና ሆኗል። በሚገርም ሁኔታ በጣም ውስን ወጣቶች ስራ ፍለጋ ጉዳያቸው አይደለም። የፈለጉትን ስራ በፈለጉበት ጊዜ መቀያየር ይችላሉ። እነሱ ከጊዚያዊ ስራ ፍለጋ አልፈው የወደፊት ትልቁን ህልማቸውን ለማሳካት በመታተር ላይ ናቸው።
ብዙሃኑስ?
ብዙሃኑማ በተለመደው መንገድ እየተጓዙ ስራ ማግኘት ፈተና ሆኖባቸዋል። ስራ ባለማግኘታቸው ደግሞ እነሱም፤ ቤተሰብም፤ ማህበረሰብም እንዲሁም ሃገርም ጭምር አላስፈላጊ ጫና ውስጥ ይገኛሉ።
አንተ ከውስኖቹ ጎራ መቀላቀል ትፈልጋለህ ወይስ በብዙሃኑ መንገድ ትቀጥላለህ? ምርጫህ ሁለተኛው ከሆነ እዚሁ ላይ አቁም።
ካልሆነ ማንበብህን ቀጥል።
በየአመቱ ብዙ ሺህ ወጣቶች ከኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲወች ተመርቀው ወደ እውነታው አለም ይቀላቀላሉ። ሆኖም በዚህ ጊዜ አንድ ወጣት የኮሌጅ ዲግሪ ስለያዘ ብቻ ስራ በቀላሉ አገኛለሁ ብሎ ማሰብ የማይቻል ሆኗል። በሁሉም የሙያ ዘርፎች በሚባል ደረጃ ስራ ማግኘት አድካሚና ረዥም ጊዜ እንደሚወስድ ይነገራል። ብዙሃኑ ወጣቶች ፈጽም የማይጠብቁት ክስተት ስለሆነ በቶሎ ስራ አለማግኘት በግልም ይሁን በቤተሰብ ደረጃ የመንፈስ ስብራት ይደርስባቸዋል።
➡️ የሚገርመው በተቃራኒው ያሉት ስራ ቀጣሪዎች ደግሞ የሰራተኛ ያለህ እያሉ ያማርራሉ። ሃላፊነት የሚሸከም፣ እምነት የሚጣልበት፤ ተገቢው የስራ ዝግጅት ያለው ወጣት ወይም ሰራተኛ የስራ ገበያው ላይ ማግኘት እንደሚቸገሩ ይናገራሉ።
ችግሩ የት ነው ያለው?