“ለራሳችሁ በላችሁት እንጂ ለእኛ ምን አተረፋችሁልን”

#አንዳንድ#ነገሮች!

✅ ሃገራችን ውስጥ ካሉ እጅጉን ከሚገርሙኝ አስተሳሰቦች አንዱ #ወጣቶች ላይ የሚሰነዘረው ወቀሳ ነው። በፖሊሲ ማእቀፍ አስቦና አልሞ ፤ ገንዘብና ጉልበት መድቦ፤ በብዙ ዓመት ድካም ትወልዱ እንዲህ እንዲሆን ከተሰራ በኋላ መልሶ ትውልዱን ( ውጤቱን) መውቀስ በምንም መልኩ ሊገባኝ አልቻለም።

✅ የሚገርመውና ተስፋ የሚሰጠኝ ደግሞ፤ እጅግ ብዙ #ወጣቶች ወቀሳው ሳይበግራቸው የማንንም ቸርነት ሳይጠብቁ ፤ ችግሮችን ለማለፍና የመፍትሄ አካል ለመሆን ጥረት ሲያደርጉ ሳይ ነው። ባናበረታቸው እንኳን ከመንገዳቸው ዞር እንበልላቸው። የእነሱ ስኬት የሁላችንም ስኬት ነውና።

Advertisements

✅ ድሮ ውይይት ታክሲ አዲስ አበባ ውስጥ በብዙ ቦታወች የታክሲ አገልግሎት ትሰጥ ነበር። እናም በአንድ ወቅት ተማሪ እያለሁ ከሃና ማሪያም ወደ ሳሪስ ለመሄድ ውይይት ታክሲ ውስጥ ገባሁ። እኔ በተቀመጥኩበት ረድፍ 5 መካከለኛ ሰወች ተቀመጥን፤ በተቃራኒው እረድፍ ደግሞ 4 ወፍራም ወፍራም ሰዎች ተቀመጡና ታክሲው መያዝ የነበረበት አንድ ተጨማሪ ሰው ቦታ ጠፋ። ረዳቱ ( ወያላው) በጣም ትንሽ ልጅ ነበር። እናም አንድ ተጨማሪ ተሳፋሪ እንዳይጨምር ቦታ የለም፤ በ9 ሰው እንዳይሄድ 10 ሰው መጫን እንዳለበት በአለቃው( ሾፌሩ ወፍራም ናቸው) ታዟል። በጣም ተቸገረና በመሃል ሳያስበው እነዚህስ ወፍራም ወፍራም ናቸው አለ። ከዛም 4ቱም ሰዎች በሚገርም ፍጥነት እንዳንተ በችጋራሙ ቀን ስላልተፈጠርን ነው ብለው ልጁ ላይ በአንድነት ጮሁበተ። ሁሉም ጸጥ አለ።

ከዛም በጣም ከመናደዴ የተነሳ፤ ለልጁም በእድሜ ቀረብ እለው የነበርኩት እኔ ስለነበርኩ፤ እና ለራሳችሁ በላችሁት እንጂ ለእኛ ምን አተረፋችሁልን አልኋቸው። በእኔ በኩል ተቀምጣ የነበረች ብቸኛዋ እናት የእኔን ሃሳብ ደግፋ በጩሀት አቀለጠችው። ሌሎችም ወደ ውይይቱ ቀስ እያሉ ገቡ። ሳሪስ እስከምንደርስ ተከራከርን ( ውይይትም አይደለች) መግባባት ግን አልነበረም።

✅ እነዚያ ሰዎች ምን አልባትም የራሳቸውን ልጅ ት/ት ቤት ልከው ነው ወደ ታክሲ የመጡት፤ ግን ለዚያ ትንሽ ልጅ ርህራሄ አልነበራቸውም። እነሱ መስራት የነበረባቸውን በዚያ ለጋ እድሜው ሃላፊነት ወስዶ ከችግሮቹ (ለዚያውም እሱ ያልፈጠራቸውን ) ለመላቀቅ ጥረት ማድረጉን እንኳን ለማሰብ አልፈለጉም። አሁንም ቢሆን ብዙ ወጣቶች ላይ እየሆነ ያለው ተመሳሳይ ነው። መንግስታዊ ስርዐቱም ቢሆን እድሎችን ሁሉ በፖሊሲና በህግ ማህቀፍ አንቆ ይዞ ስለ ወጣቶች የመናገር ሞራል የለውም።

Advertisements

🟡 #ወጣቶች ግን በርቱ፤ ችግሮቹን ብቻ ሳይሆን መልካም አጋጣሚወች ላይ ትኩረት አድርጉ። በእርግጠኛነት ከእኛ የተሻለ ጊዜ ይኖራችኋል።

End.  One final Thought: What ever we do to succeed,

Showing Up Matters

We write and Podcast on career growth & personal development and inspire the youth to take action. 

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.